Image may be NSFW.
Clik here to view.ጅግጅጋ(cakaaranews)ረቡዕ፤ሐምሌ 25/2010 ዓ.ም በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መዲና ጅግጅጋ ሐምሌ 28 ቀን ጀምሮ በክልሉ ታላቅ የሰላምና አንድነት የጋራ የምክክር መድረክ የሚካሄድ ሲሆን በዚህም በሁሉም የዓለም ክፍል ለሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች በአጠቃላይ በዚህ የጋራ የምክክር መድረክ ላይ እንዲገኙ በሃገር ሽማግሌዎች፣ ኡጋሶችና የጎሳ መሪዎች በኩል ጥሪ መተላለፉ ይታወሳል።
Image may be NSFW.
Clik here to view.Image may be NSFW.
Clik here to view. በዚህም መሠረት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ አብዲ መሀሙድ ዑመር መልዕክት “ሁላችሁም የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ተወላጅ የሆናችሁና በሃገር ውስጥና በውጭ ሃገራት ለምትኖሩ ክልሉ በሰላም፣ ልማትና አንድነት የጋራ የምክክር መድረክ በማዘጋጀት ላይ የሚገኝ ሲሆን ይህ ጉዳይ ይመለከተናል የምትሉ የክልሉ ምሁራን፣ የፖለቲካ ተፎካካሪ መሪዎችና ግለሰቦች ሁሌም ሰላም ወዳድ የሆነው ህዝባችንን እናንተኑ ለማስተናገድ ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም እየጠበቃችሁ ስለሆነ በዚህ የጋራ መድረክ እንድተገኙ ስል በራሴ፣ በክልሉ ህዝብና መንግሥት ሥም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።” ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።